የሁልባራግ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፓርቲ ኮሚቴ የ2019 በጀት አመት  የዝግጅት ምዕረፍ  ተግባራትን ገመገመ !
የሁልባራግ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፓርቲ ኮሚቴ የ2019 በጀት አመት የዝግጅት ምዕረፍ ተግባራትን ገመገመ !
ሐምሌ 28/2018 ዓም የሁልባራግ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት
በስልጤ ዞን የሁልባራግ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፓርቲ ኮሚቴ የ2019 በጀት አመት የዝግጅት ምዕረፍ ተግባራትንና ወቅታዊ የንቅናቄ አጀንዳዎችን ገመገመ።
የውይይት መድረኩን የመሩት የሁልባራግ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙላጎ ከይረዲን እንዳነሱት ባለፈው በጀት አመት ከወረዳ እስከ ቀበሌ የፓርቲ አደረጃጀቶችን በማጠናከር አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸው ጉድለቶች ለቀጣይ የዕቅድ አካል ተደርገው መስራት እንደሚጠበቅ አንስተዋል።
ባለፈው በጀት አመት የህዝብ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጉደዮችን በፓርቲው መሪነት በመፈፀም የህብረተሰብን ተጠቃሚነት መከናወናቸውን ያነሱት አቶ ሙላጎ የነበሩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል ጉድለቶችን በዝግጅት ምዕራፍ የዕቅድ አካል ተደርገው እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የፓርቲ ኮሚቴው የ2019 በጀት አመት በዝግጅት ምዕራፍ እየተሰሩ የሚገኙ ተግባራትንና የንቅናቄ ስራዎች ያሉበትን አፈፃፀም በሁሉም ዘርፍ በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በመጨረሻም በዝግጅት ምዕራፍ እስከ አባል ጠንካራ ዕቅድ ማቀድ፣ አዳድስ አባላትን ከማፍራት፣ የፓርቲ አደረጃጃቶችን በየደረጃው በማጠናከር እንዲሁም የብልጽግና ህብረት ጽ/ቤት ላይ መረጃን የማደረጃት ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል።